Saturday, November 23, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ተግባራዊ ላይደረጉ እንደሚችሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ተግባራዊ ላይደረጉ እንደሚችሉ በዛሬው ሳምንታዊ መግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ከሰሞኑ በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት የተኩስ አቁም ማድረጉ የውጭ ሀገራት እና ተቋማት በጥሩ ጎን እንደተመለከቱት ገልጸዋል፡፡

የውጭ መንግስታት እና ተቋማት በትግራይ ክልል ጦርነቱ ከተጀመረ ግዜ አንስቶ ሲጠይቁ የነበሯቸው ነገሮች ምላሽ አግኝነተዋል ያሉት ቃል አቀባዩ፣ ሀገራት እና ተቋማቱ ትግራይን ለእርዳታ ክፍት አድርጉ ብለው አድርገናል፤ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራም ይደረግ ተብሎ መፈጸሙን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም አሁን ደግሞ የተኩስ አቁም መደረጉም አንዱ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አምባሳደር ዲና፣ ኢትዮጵያ ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች ይሳሳሉ ያሉ ሲሆን፣ ቀድሞውኑ የተጣሉ ማዕቀቦችም ገቢራዊ አይሆኑም የሚል ተስፋ እንዳለ ገልፀዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img