Saturday, November 23, 2024
spot_img

መንግሥት በአብዬ ግዛት ያለው ሰላም አስከባሪ የሚወጣ ከሆነ ለከፈለው መስዋዕትነት ክብር ተሰጥቶት ሊሆን ይገባል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ቦታውን ለቆ የሚወጣ ከሆነ ለከፈለው መስዋዕትነት ተገቢውን ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይህን የተናገሩት በዛሬው እለት በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት፣ በሱዳን አብዬ ግዛት የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ኃይል ለከፈለው መስዋዕትነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስጋና ማቅረቡን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሀላፊ ጋር በተወያዩበት ወቅት ተናግረዋል ነው ያሉት፡፡

ቃል አቀባዩ አቶ ደመቀ መኮንን ውይይት ያደረጉት ከመንግሥታቱ ድርጅት የምሥራቅ አፍሪካ የፖለቲካ፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች እና ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር ግርሃም ሜይትላንድ ጋር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በአብዬ የሰላም ማስከበር ዙሪያ ከተመድ የስራ ኃላፊ ጋር በተወያዩበት ወቅት፣ አብዬ ስላለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ማብራሪያ ሰጥተዋል ያሉ ሲሆን፣ ውይይቱ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ ስትራቴጂክ ግምገማና በተልዕኮውን መልሶ ማዋቀር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።

በወቅቱም አቶ ደመቀ ሰላም አስከባሪ ኃይሉ በአብዬ ግዛት መቆየት እንዳለበት መናገራቸው ተገልጿል። ይሉ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባም አቶ ደመቀ ተናግረዋል፡፡ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ ከስፍራው መውጣት በአካባቢው ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና ግጭት እንደሚያባብሰውም ገልፀዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከአብዬ ግዛት እንዲወጣ ጥያቄ ማቅረቧን በተመለከተም፣ ሰላም አስከባሪ ኃይሉ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በደረሱት ስምምነት መሰረት በተመድ ስር በስፍራው መሰማራቱን አስረድተዋል፡፡

አቶ ደመቀም የኢትዮጵያ ወታደሮች ጦርነትን ለመከላከል ዋጋ እየከፈሉ መሆኑን አንስተው፣ መውጣታቸው አስፈላጊ ከሆነም በባለድርሻ አካላት አስፈላጊው መግባባት ተደርሶበት እና ተገቢውን ክብር በጠበቀ ሁኔታ መሆን እንደሚገባ መናገራቸውን አምባሳደር ዲና መናገራቸውን የአል ዓይን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img