Saturday, October 12, 2024
spot_img

ሳዑዲ ዐረቢያ በብርቱካን ጭነት ወደ አገሬ ሊገባ ነበር ያለችውን በርከት ያለ ‹‹አምፌታሚን›› የተሰኘ እንክብል መያዟን አስታወቀች

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― ሳዑዲ ዐረቢያ ከብርቱካን ጭነት ጋር ባንድነት ተደርጎ ወደ አገሬ ሊገባ ነበር ያለችውን 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብዛት አምፌታሚን የተሰኘ እንክብል (ያገሩ ሰዎች እንደሚጠሩት ካታጎን) መያዟን ማሳወቋን አል አረቢያን ዋቤ አድርጎ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በጂዳ ወደብ በኩል በብርቱካን ካርቶን ደርሷል የተባለው ይኸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው አምፌታሚን የተሰኘው እንክብል፣ በጉምሩክ ሰዎች የኤክስ ሬይ ፍተሻ ወቅት መያዙን ባለሥልጣናት አሳውቀዋል፡፡

ይኸው እንክብል ከየት እንደተነሳ እስካሁን ድረስ ያልተገለጸ ቢሆንም፣ አገሪቱ ከቀናት በፊት ከሊባኖስ የተነሳ ሌላ 14 ሚሊዮን የእንክብሉን ጭነት ይዛ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

የአገሪቱ ባለሥልጣናት የዚህን እንክብል ጭነት መድረስ ሲጠባበቁ ነበሩ ያሏቸውን በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን መናገራቸውም ተሰምቷል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ ከዚህ ቀደም ከሊባኖስ ወደ አገሯ መድሃኒት ለማስገባት ከተደረገ ሙከራ በኋላ፣ ከሊባኖስ የሚገቡ ምርቶች ላይ እቀባ ማድረጓንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በብርቱካን ካርቶን ተሸፋፍኖ ሊገባ ነበር የተባለው ማዕከላዊ የነርቭ ሥርዓትን አነቃቂ ነው የሚባልለት አምፌታሚን የተሰኘው እንክብል፣ ተደጋግሞ ከተወሰደ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ሊዳርግ የሚችል እና በጊዜ ሒደት ሱስ የመሆን አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img