Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሐጫሉ ሁንዴሳ አዲስ አልበም ‹‹ማል ማሊሳ›› የሽያጭ ሰንጠረዡን እየመራ ይገኛል

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ተመርቆ በበይነ መረብ ለገበያ የቀረበው የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ‹‹ማል መሊሳ›› የተሰኘ ርእስ ያለው የሙዚቃ አልበም፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሳምንታዊ የሽያጭ ሰንጠረዦችን እየመራ ይገኛል፡፡

ዓለም አቀፉን የኢንተርኔት ሙዚቃ መገበያያ አይቱንስን ጨምሮ በአገር ውስጡ አውታር የሙዚቃ መረብ ሽያጭ አንደኛ ደረጃን የያዘው አልበም፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22፣ 2012 የተገደለው የአርቲስቱ 3ኛ የሙዚቃ አልበም ሲሆን፣ 14 ሙዚቃዎችን ይዟል፡፡

አልበሙ ከኢንተርኔት ገበያው በተጨማሪ በሲዲ ደረጃ 500 ሺሕ ቅጂ ታትሞ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መሠራጨቱ ተሰምቷል፡፡ አዲስ ዘይቤ ድረ ገጽ የአልበሙ የሽያጭ አስተባባሪ አቶ አመንሲሳ ኢፋ ነግረውኛል እንዳለው፣ በኢንተርኔት ሽያጭ አንደኝነትን የተቆናጠጠው አልበም፣ በሲዲ በብር 100 እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ባለው መረጃ አልበሙ በአይቱንስ በኩል በተለያዩ የዓለም አገራት ባለው ሽያጭ ያለው ደረጃ ሲታይ በአውስትራሊያ፣ በካናዳ በተባበሩት ዐረብ ኢሚሬቶች እና በአሜሪካ አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ በብሪታንያ 7ኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት እስከ 10 ባሉ ደረጃዎች ላይ መቀመጥ በመቻሉ፣ በአማካይ ድምር ሲሰላ 1ኛ ሆኖ መምራት እንደቻለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በሌላ መረጃ ሐሊፌክስ የተባለው የካናዳ ግዛት ድምጻዊው ተገደለበት ሰኔ 22 (የፈረንጆቹ ጁን 29) የኦሮሚያ ቀን ተብሎ እንዲሰየም መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

በዚህ እለት ካናዳዊያን ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ፣ ባህል እና እሴት የሚያውቁት እንዲሁም እውቅና የሚሰጡበት ቀን ይሆናል ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img