Saturday, October 12, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሠርተዋል ያለቻቸውን ልኡል መሐመድ ቢን ዛይድን አወደሰች

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― የአሜሪካ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ የሆኑት ጃኪ ሱሊቫን የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት ልኡል መሐመድ ቢን ቢን ዛይድ ጋር ስልክ መትተው፣ በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲበጅለት ሠርተዋል በሚል ውዳሴ መቸራቸውን ዋይት ሐውስ አሳውቋል፡፡

በዚሁ የስልክ ቆይታ ወቅት ሁለቱ ሰዎች በትግራይ ክልል የሕይወት አድን እርዳታ አንገብጋቢነት ላይ መነጋገራቸውም ተገልጧል፡፡

አሁን በአሜሪካ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተኩስ አቁም እንዲታወጅ ሠርተዋል ተብለው የተወደሱት መሐመድ ቢን ዛይድ የሚመሯት የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ በትግራይ ጦርነት ጅማሮ ተሳትፎ አላት በሚል በክልሉ ተቃዋሚ ፖርቲዎች ወቀሳ የቀረበባት ነበረች፡፡

በወቅቱ የቀረበባት ወቀሳ ላይ ምላሽ ያልሰጠችው አቡ ደቢ፣ ከሰሞኑ የፌዴራል መንግሥት የተኩስ አቁም ሲያውጅ ውሳኔውን ካወደሱ መካከል ትገኝበታለች፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img