Wednesday, December 4, 2024
spot_img

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሠራተኞች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ እየጠበቁ ይገኛሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― ከቀናት በፊት በመንግሥት ድጋፍ ከትግራይ ክልል በየብስ ትራንስፖርት ተጓጉዘው አዲስ አበባ ደርሰዋል የተባሉት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ ቀጣይ ዕጣ ፋንታቸውን ለመወሰን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽ እየተጠባበቁ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ባልታሰበና ምሥጢራዊ ጭምር በነበረ ዝግጅት ከትግራይ ክልል መውጣታቸው የተነገረው የጊዜያዊ አስተዳደር መሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ሥፍራዎች በተዘጋጀላቸው ጊዜያዊ ማረፊያ እንደሚገኙ ዋዜማ ራድዮ አረጋግጫለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

ቀደም ባሉት ወራት ከጊዜያዊ አስተደደሩ መሪዎች መካከል አንዳንዶች የመንግሥትንና የመከላከያን ምሥጢሮችን ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ሲፋለም ለሰነበተው ሕወሓት ያቀብላሉ በሚል በአመራሮቹ መካከል ውጥረት ሰፍኖ፣ ሙስና እና ብልሹ አሠራር ስፍኗል በሚልም አመራሩን እስከመበወዝ የደረሰ ርምጃ ተወስዶ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

ወትሮም እንደነገሩ ነበሩ የተባሉት አመራሮቹ፣ አሁን የቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የአንዳንድ ትግራይ የቀሩ የበታች አመራሮች ደኅንነት እንደሚያሰጋቸው እየተናገሩ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ቀናት ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ውሳኔ እየተጠባበቁ መሆኑን አመራሮቹ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተቋቋመው የአገር መከላከያ ሠራዊት የክልሉን መቀመጫ መቀሌ ከተማን ከተቆጣጠረና የሕወሓት አመራር ወደ በረሀ ከሸሸ በኋላ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img