Saturday, October 12, 2024
spot_img

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በመቐለ ለሲቪል ዜጎች ከለላ እንዲሰጥ አሳሰበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 23፣ 2013 ― አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቀሌ ከተማን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሉ ሲቪል ዜጎች አስቸኳይ ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል፡፡

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ አካባቢ ምክትል ዳይሬክተር ሣራ ጃክሰን ባወጡት መግለጫ፣ ድርጅታቸው ትግራይ ውስጥ የሲቪል ዜጎች ደኅንነት በብርቱ እንዳሳሰበው ነው ያመለከቱት፡፡

ሲቪሉ ኅብረተሰብ ለወራት ጦርነቱን እና የመብት ጥሰቶችን እንዲሁም የጦር ወንጀልን ተቋቁሞ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት አካባቢውን ለቅቀው ሲወጡ እና የክልሉ ኃይል በስፍራው ሲተካ ለሲቪሎች ተገቢውን ከለላ ማረጋገጥ መሠረታዊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡

በመሆኑም «ቀጣይ ግድያ እና የጦር ወንጀል ከመፈጸም ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ፤ በተለይም የበቀል ጥቃቶች በወታደሮቻቸውም ሆኑ ከእነሱ በወገኑ ሚሊሺያዎቻቸው እንዳይፈጸም ጥሪ እናቀርባለን» ብለዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ኢንተርኔትን ጨምሮ የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ መረጃ ለማግኘት እንቅፋት መሆኑንም አምኔስቲ በመግጫው ጠቁሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img