Monday, October 7, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ የተኩስ አቁም መደረጉ መልካም ርምጃ መሆኑን ገለጸች

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 23፣ 2013 ― የፌዴራል መንግስት በትግራይ ጉዳይ በተናጠል የተኩስ አቁም ርምጃን መውሰዱ ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መግለጫ አውጥቷል፡፡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ በቤቱ ቃል አቀባይ በኔድ ፐራይስ ባወጣው መግለጫ የተኩስ አቁም ሂደቱ ግጭትን ካስቆመ፣ እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፎች ያለ ገደብ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እንዲደርስ ለማድረግ ካስቻለ ውጤታማ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ “ግጭቱን የሚያስቆም ከሆነ” በአዎንታ የሚታይ መሆኑን ገለጸች::

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለመጠበቅ እንዲሁም በትግራይ መረጋጋት እንዲመጣ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሜሪካ ጠይቃለች፡፡ ሁሉም ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግን በጥብቅ እንዲያከብሩ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ተጠያቂነት እንዲኖሩባቸው መደረግ እንደሚገባ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

አሜሪካ በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በትብበር ለመስራት ዝግጁነት እንዳላትም ገልጻለች፡፡

የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው እርምጃ ግጭቱን ለማቆም የሚያስችል ትክክለኛ እርምጃ ነው ብሏል፡፡

ለተወሰደው የተኩስ አቁም እርምጃ እውን መሆንና በትግራይ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የመንግስት ባለስልጣናት ሊሰሩ እንደሚገባም የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ሞሀማት ጥሪ አቅርቧል፡፡ የትግራይን ግጭት ጉዳይ ፖለቲካዊ መፍትሄ አንደሚሻና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰላም ለማስፍን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኑንም ሊቀ መንበሩ አስታውቀዋለ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከጊዝያዊ አስተዳደር ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽና ባወጣው መግለጫ “በተናጠል ተኩስ ለማቆም” ወስኗል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img