Saturday, November 23, 2024
spot_img

ዶክተር ደብረጽዮን የፌዴራል መንግሥትን የተኩስ አቁም እንደማይቀበሉት መናገራቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 23፣ 2013 ― ከፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት ውስጥ የሚገኘው ሕወሃት አመራሮች መካከል እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ባለፉት ጊዜያት ከሚዲያ የተሰወሩት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን እንደማይቀበሉት መናገራቸውን ለሕወሃት ሰዎች ቅርብ እንደሆነ የሚነገርለት የኖርዌይ ዜግነት ያለው የግጭት አጥኚው ጄቲል ትሮንኖቮል በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

የግጭት አጥኚው ጄቲል እንዳሰፈረው ከሆነ፣ ዶክተር ደብረጽዮን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የመገናኛ አገልግሎት አቋርጧል ያሉት የፌዴራል መንግሥት የተኩስ አቁም ያወጀው ‹‹ጊዜ ለመግዛት እና አሰላላፍ ለማስተካከል ነው›› ብለው ያስባሉ፡፡

በመሆኑም ዶክተር ደብረጽዮን የተኩስ አቁም መታወጁን በቁም ነገር የሚወስዱት እንዳልሆነ ነው የሠፈረው፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከትላንት በስትያ ግንቦት 21 ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀረበለትን ጥሪ ተከትሎ በትግራይ የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁ መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img