Monday, September 23, 2024
spot_img

ፊንላዳዊቷ ጋዜጠኛ ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሚገኝ ገለጸች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 22፣ 2013 ― ባሳለፍነው እሑድ የሕወሃት ኃይሎች አመራሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት ገጠራማ ሥፍራ ድረስ በማቅናት ቃለ ምልልስ የሠራችው የፊንላንድ ዜግነት ያላት ሊሴሎተ ሊንድስትሮም የተባለችው ጋዜጠኛ፣ በበይነ መረብ ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሚገኝ አሳውቃለች፡፡

ጋዜጠኛዋ በትዊተር ባሰፈረችው መልእክት እንዳሳወቀችው፣ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተገኘችው ለመዘገብ የሥራ ፈቃድ አግኝታ መሆኑን ያመለከተች ሲሆን፣ ሥራዋ ከረድኤት ድርጅቶች ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለም ነው የገለጸችው፡፡

አሁን ማስፈራሪያ እየደረሰብኝ ነው ያለችወ ጋዜጠኛ ሊሴሎተ ሊንድስትሮም፣ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ካደረገችው ቃለ ምልልስ ጋር ተሠራጭቶ የነበረው ፎቶዋ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች በሥፋት መነጋጋሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛዋ ባጠናቀረችው ዘገባ፣ አቶ ጌታቸው በትግራይ ሥሙ ካልተጠቀሰ ሥፍራ ከገበሬ ቤተሰብ ጋር ሕይወት እየገፉ የሕወሃት ኃይሎችን እየመሩ መሆናቸው ሠፍሮ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img