Saturday, October 5, 2024
spot_img

አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ 7 አገራት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲመክር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 22፣ 2013 ― አሜሪካ እና እንግሊዝን ጨምሮ ሰባት አገራት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በግልጽ እንዲመክር መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

ምክር ቤቱ ይሰብሰብ የሚለውን ጥሪ ያስጀመሩት የምክር ቤቱ ቋሙ አባል አገራት የሆኑት አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከአየርላንድ ጋር ባንድነት መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፣ ኋላም ሌላኛዋ ቋሚ የምክር ቤቱ አባል ፈረንሳይ እንዲሁም ኢስቶንያ እና ኖርዌይ ጥሪውን ተቀላቅለዋል፡፡

ሆኖም ይኸው ጥሪ በሌሎች የፀጥታ ምክር ቤቱ አባል አገራት ባለማግኘቱ አገራቱ ምክር ቤቱ እንዲያደርግ የጠየቁት ግልጽ ስብሰባ ሊካሄድ እንደማይችል ነው የተነገረው፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ ላይ በዝግ ሲመክር መሰንበቱ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img