Saturday, October 12, 2024
spot_img

በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረገው አፈሳ ጋብ ቢልም ሙሉ በሙሉ አለመቆሙ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 21፣ 2013 ― ባለፉት ሳምንታት በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውን ላይ የሚካሄደው አፈሳ እና እንግልት ጋብ ቢልም፣ አሁንም ሙሉ ለሙሉ አለመቆሙን አምባ ዲጂታል በአገሪቱ ከሚገኙ የኢትዮጵያውያኑን ጉዳይ ከሚከታተሉ ምንጭ ሰምቷል፡፡

እንደ ምንጫችን ከሆነ ጋብ ብሏል ያሉት የጅምላ እስር ባለመቆሙ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የሚውሉ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ከሆኑ አሻራ ሰጥተው እንደሚለቀቁና ሕጋዊ ፍቃድ የሌላቸውን ግን እዚያው እየቆዩ ይገኛሉ፡፡

ስደተኞቹን በተመለከተ ከአገሪቱ መንግሥት ጋር እየተነጋገረ እንደሚገኝ የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር፣ ከባለፈው ቅዳሜ አንስቶ ዜጎችን እየመለሰ እንደሚገኝ የተናገረ ሲሆን፣ ምንጫችን እንደነገሩን አሁን ወደ አገር ቤት እየተመለሱ የሚገኙት ረዥም ጊዜ በአገሪቱ የቆዩት ናቸው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ በትላናትናው እለት 2 ሺሕ ሰ57 ዜጎች ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img