Saturday, October 12, 2024
spot_img

በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አማራጭ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 19፣ 2013 ― የመከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ከሱዳን እና ከግብፅ ጋር አለመግባባት ቢፈጠርም ኢትዮጵያ በወታደራዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት እንደሌላት ገልጸዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ይህን የተናገሩት በሩስያ ሞስኮ በ9ኛው የዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኃላ ከሩስያው አር ቲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ነው፡፡

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ከግድቡ ጋር በተገናኘ መፍትሄው ወታደራዊ ሊሆን አይችልም ያሉ ሲሆን፣ ከሁሉ የተሻለው በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገው ውይይቱ ነው ብለዋል።

ግብጾችን በተመለከተም ‹‹የግብፅ ወገን ችግሩን በድርድር መፍታት አይፈልጉም፤ ለውይይት ይመጣሉ ሁሉንም ሐሳብ ውድቅ ያደርጋሉ። በእኔ ምልከታ የተሻለው መፍትሄ ድርድር ነው፣ ችግሩን በወታደራዊ መንገድ መፍታት አይችሉም›› ሲሉ ተናግረዋል።

ሌተናል ጄኔራሉ ግብጾች ግድቡን ለማጥቃት አይሞክሩም፣ ቢሞክሩት እንኳን ችግሩን ሊፈቱ ወይም ግድቡን ሊያጠፉት አይችሉም፣ ግድቡ በቦንብ እና በተዋጊ ፕሌኖች ሊወድም አይችልም የግድቡን ጥንካሬ እነሱም ያውቁታል›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img