Saturday, October 12, 2024
spot_img

አሜሪካ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ባልደረቦች ግድያ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠየቀች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 19፣ 2013 ― የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ በትላንትናው እለት በትግራይ ክልል በሞቱ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ባልደረቦች ግድያ እጅጉን ማዘኑን በመግለጽ፣ ግድያው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጥሪ አቅርቧል፡፡

መስሪያ ቤቱ በረድኤት ሠራተኞች ላይ የሚፈጸም ግድያ በማንኛውም መንገድ ምክንያት ሊሰጠው የሚገባ እንዳልሆነና በአስቸኳይ መቆም ያለበት መሆኑን አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የረድኤት ሠራተኞችን ደኅንነት የመጠበቅና የልተገደበ ድጋፍ እንዲደርስ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት አጽንኦት የሰጠው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ በክልሉ ረሐብን ጨምሮ ሌላ ስቃይ እንዳይከተል እንደ ቀደሙ ጊዜያት ሁሉ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

በትላንትናው እለት በአብይአዲ አካባቢ ተፈጽሟል ለተባለው የሦስት ረድኤት ሠራተኞች ግድያ የፌዴራል መንግስት ሕወሃትን ተጠያቂ ማድረጉ መነገሩ ኤዜነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img