Saturday, October 12, 2024
spot_img

የፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ኢሶዴፓ በደቡብ ክልል በድጋሚ ምርጫ እንዲካሔድ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 19፣ 2013 ― አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል የተካሔደውን ምርጫ ሰርዞ በድጋሚ ምርጫ እንዲያካሒድ ጠይቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ ፓርቲው በሰጠው መግለጫ፣ በዋናነት በተወዳደረበት በደቡብ ክልል በምርጫው ሂደት በርካታ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት አስታውቋል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በምርጫ ቦርድ የተመደቡ ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ እንዲሁም የፀጥታ አካላትም ጭምር ከገዢው ፓርቲ ጋር ወግነው ሲሰሩ እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ በመግለጫቸው በአንዳድ አካባቢዎች ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ የምርጫ ጣቢያዎች ተቀምጠዋል ያሉ ሲሆን፣ በአካባቢው ተወካይ ማስቀመጥ እንዳልተቻለም ገልጸዋል፡፡ የጠቀሱት ጉዳይ ስለመፈጸሙ አብነት፣ የዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ በሐዲያ ዞን በሲቄ ጣቢያ የድምጽ ሂደት መጀመሩ በፊት የተሞሉ ሳጥኖች ነበሩ ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፣ አምስት የምርጫ ሳጥኖችም እንደተሰበሩ ተናግረዋል፡፡

በምርጫው ማጭበርበር ሥሙ የተነሳው የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ፣ በኢሶዴፓ የቀረበውን ክስ እንደማይቀበለው መግለጹን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል፡፡

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን በሰጡት መግለጫ በፓርቲዎች በርካታ አቤቱታዎች መቅረባቸውን እና ቦርዱ ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img