Saturday, October 12, 2024
spot_img

አሜሪካ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስጠበቅ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር የግድ ነው አለች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 19፣ 2013 ― አንቶንዮ ብሊንክን የሚመሩት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስጠበቅ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር የግድ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መስሪያ ቤቱ በሳምንቱ መጀመሪያ የተካሄደውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተበት መግለጫው፣ ምርጫው ኢትዮጵያ ከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ ባለችበት እና የምርጫው ሂደት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻና ፍትሐዊ ባልሆነበት ሁኔታ መካሄዱን ገልጧል፡፡

በተጨማሪም የታወቁ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫው አለመሳተፋቸውን ያነሳው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፣ የአገሪቱን ሉአላዊነት፣ አንድነትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት ለማስጠበቅ ሁሉን ያማከለ ጥረት በማድረግ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ የግድ መሆኑን ነው ያመለከተው፡፡

በዚህ የድህረ ምርጫ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ መሪዎች ከጠብ ጫሪነት እንዲርቁ መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡ በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፣ ‹‹በትግራይ ክልል የቀጠለው ግጭት እና ሰብዓዊ ቀውስ አፋጣኝ ተግባራዊ እርምጃ የሚጠይቅ›› መሆኑን አስታውቋል፡፡

እንደ ቀደሙት ጊዜያት ሁሉ በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ መሬት እንዲለቅ፣ የተፈፀሙ ከፍተኛ ወንጀሎች ላይ ምርመራ እንዲደረግና ያልተገደበ የሰብዕዊ ርዳታ እንዲደረግም ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img