Monday, September 23, 2024
spot_img

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሦስት ባልደረቦቹን ተገድለው ማግኘቱን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 19፣ 2013 ― ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሦስት ባልደረቦቹን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተገድለው ማግኘቱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሐኪሞች ቡድኑ ተገደሉብኝ ያላቸው ባልደረቦቹ የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪዋ ማሪያ ሄርናንዴዝ፣ ምክትሏ ዮሐንስ ሐለፎም እና አሽከርካሪው ቴድሮስ ገብረማርያም ናቸው፡፡

የስፔን ዝግነት ያላት የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪዋ፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት በድርጅቱ የቆየች ሲሆን፣ ሁለቱ ኢትዮጵያውን ባለፈው ጥር እና ግንቦት ወር ላይ የድርጅቱ አባል የሆኑ መሆናቸውን ገልጧል፡፡

ግድያውን አስመልክቶ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮለኔል ጌትነት አዳነ በትግራይ ክልል አብይአዲ አካባቢ የ3 ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሰራተኞችን ሕወሃት ከመኪናቸው አስወርዶ እንደገደላቸው አስታውቀዋል፡፡

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ‹‹በየትኛውም መመዘኛ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ሰዎችን መግደል ተቀባይነት የሌለውና ሰላም ወዳድ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጭካኔ ነው›› ብለዋል።

በተመሳሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአቢአዲ አካባቢ በሦስት ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች ላይ ሕወሃት ግድያ መፈጸሙን ያመለከተ ሲሆን፣ የረድኤት ሠራተኞች በነዚህ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ በጸጥታ አካላት እንዲታጀቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጥቃት አድርሰዋል የተባሉት የሕወሃት ኃይሎች በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img