Thursday, November 28, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 18፣ 2013 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ እንደገና ባገረሸው ውጊያ ምክንያት ወደ መቐለ የሚያደረገውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ማቋረጡ ተነግሯል። አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው ከማክሰኞ ሰኔ 15 ጠዋት ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ እና የጉዞ ወኪል ሰራተኞች ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

በትላንትናው እና በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ፤ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በረራ የነበራቸው መንገደኞች ከጉዟቸው መስተጓጉላቸውን ዘገባው አክሏል።

ለተጓዦቹ በረራ መሰረዙ የሚነገራቸው አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ እንደሆነ በመቐለ አየር ማረፊያ የሚሰሩ አንድ ባለሙያ ገልጸዋል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ እንደተናገሩት፤ የመጨረሻው በረራ የተደረገው 53 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ወደ አዲስ አበባ ማክሰኞ ከምሽቱ 12 ጉዞውን ባደረገው አውሮፕላን ነው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል በእሳት የተያያዘ አንድ አውሮፕላን ወደ መሬት ሲወርድ አሳይቷል።

ከዚያ በኋላ የነበሩት በረራዎች የተቋረጡት፤ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ አንድ የጦር አውሮፕላን ግጀት በተባለ አካባቢ በአየር ላይ ተመትቷል መባሉን ተከትሎ መሆኑን እኚሁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ያብራራሉ።

አውሮፕላኑ በሕወሃት ኃይሎች በአየር መቃወሚያ መመታቱ ቢገለጽም፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቃል አቃባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ይህንን አስተባብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img