Monday, September 23, 2024
spot_img

በደቡብ ክልል በምርጫ ተወዳዳሪ የነበሩ ፓርቲዎች ያወጡት መግለጫ የፓርቲያቸውን አቋም እንደማያንጸባርቅ የወሕዴግ ሊቀመንበር ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 18፣ 2013 ― በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በምርጫ ተወዳዳሪ የነበረው የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ተክሌ ቦረና በምርጫው ተወዳዳሪ የነበሩ ስምንት ፓርቲዎች፣ ምርጫውን በተመለከተ ያወጡት መግለጫ የፓርቲያችንን አቋም አያንጸባርቅም ብለዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ይህን ቢሉም ኢዜማ እና ነእፓን ጨምሮ ስምንት ፓርቲዎችን የያዘው ስብስብ ለምርጫ ባስገባው የቅሬታ ደብዳቤ ላይ፣ ፓርቲያቸው ዶክተር ብስራት ኤልያስ በተባሉ ግለሰብ መወከሉን ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

ሆኖም አቶ ተክሌ ቦረና ለአዲስ ዘይቤ እንደገለጹት፣ በደብዳቤው የተገለጸው የወላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር እንደ ፓርቲ ሳይሆን፣ ‹‹በስሜት ተነሳስተው በዞኑ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው መግለጫውን የሰጡት›› ብለዋል፡፡

አክለውም ‹በምርጫው ሂደት ጥቃቅን ችግሮች ቢኖሩም፣ ለሀገሪቱ ሰላም ሲባል በይደር አልፈነዋል›› ማለታቸው ተመላክቷል፡፡

የወላይታ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን ጨምሮ ስምንቱ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ በጻፉት ደብዳቤ፣ በወላይታ ዞን በሰባት የምርጫ ክልሎች በተካሄደው ምርጫ፣ የገዢው ፓርቲ ሰዎች የምርጫ ታዛቢዎችን ከምርጫው ሂደት ማባረር፣ ድብደባ ማድረስ እና አፍነው መውሰድ፣ ፓርቲዎችን በህገ ወጥ መንገድ ከውደድር ውጪ ማድረግ፤ የምርጫ አስፈጻሚዎች ለመራጮች የገዢውን ፓርቲ ምልክት በመናገር እንዲመርጡ ገለጻ ማድረግ እና ሌሎችንም በመዘርዘር ቅሬታ አቅርበው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img