Saturday, October 12, 2024
spot_img

በኢትትጵያ ብሔራዊ መግባባት እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 18፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያን ልኡክ ጨምሮ የ12 አገራት ኤምባሲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ምርጫ ማድረግ ብቻውን ዴሞክራሲን ስለማያመጣ ብሔራዊ መግባባት እንዲካሂድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጀርመን፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዑክ ያሉበት ቡድን በመግለጫው፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ተወጥራ ባለችበት ሁኔታ ምርጫውን ማካሄዷን አንስተዋል፡፡

አገራቱ በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ምርጫው በተሻለ ሁኔታ እንዲካሄድ ማድረግ ችሏል ላሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሙገሳ ሰንዝረዋል፡፡

ጨምረውም በምርጫው ወቅት ያጋጠማቸውን ችግር ተቋቁመው ምርጫው እንዲጠናቀቅ ያደረጉትን አካላት እና የሲቪክ ማኅበራት እንዲሁም መራጮችንም በበጎ ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ምርጫ ማድረግ ብቻውን ዲሞክራሲን ሊያረጋግጥ እና የፖለቲካ ችግሮችን ሊፈታ አይችልም ያሉት አገራቱ፣ መንግስት እና የሚመለከታቸውን አካላት ያካተተ ብሔራዊ መግባባት ሊካሄድ እንደሚገባ ነው ያመለከቱት፡፡

አገራቱ ትግራይን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ያለውን ችግር ለመፍታት መፍትሔው ይህ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img