Friday, November 22, 2024
spot_img

ሂዩማን ራይትስ ዎች የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ለተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲሰፍን እገዛ እንዲያደርግ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 18፣ 2013 ― ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ለተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲሰፍን እገዛ እንዲያደርግ መጠየቁ ተሰምቷል፡፡

ድርጅቱ ይህን የጠየቀው ከሰሞኑ በአሜሪካ እና አውሮፓ ጉባኤ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ድጋፍ እንዲደደረግበት በጠየቀበት ወቅት ነው፡፡

ድርጅቱ አቅርቦታል በተባለው ባለ 27 ገጽ ሪፖርት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በማይናማር በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች እና በሮሂንግያ ጭፍጨፋ ዙሪያ ነው፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ የዓለም አቀፉን የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና የመከላከለኛወ አፍሪካ የልዩ ወንጀሎች ችሎትን እንዲደግፍም ነው የጠየቀው፡፡

በሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ለተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲሰፍን እገዛ እንዲያደርግ የተጠየቀው የባይደን አስተዳደር፣ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በጥቅምት ወር መጨረሻ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ተፈጽሟል ላላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የተለያዩ መግለጫዎችን ሲያወጣ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባ ማድረጉም አይዘነጋም፡፡

በተጨማሪ የአሜሪካ መንግሥት ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ከመቐለ በስተምዕራብ 20 ኪሎ ሜትር ላይ ቶጎጓ በሚባል ሥፍራ ተፈጽሟል ባለው የአውሮፕላን ጥቃት፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንጹሐን ጉዳት እንደደረሰባቸው በመጥቀስ ጥቃቱን አውግዟል፡፡

ይህንኑ የደረሰውን ጥቃት በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲደረጉም ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img