Saturday, November 23, 2024
spot_img

የኦነግ ከፍተኛ አመራሩ በፍርድ ቤት ነጻ ተብለው ቢለቀቁም በድጋሚ ታፍነው የደረሱበት አለመታወቁ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 18፣ 2013 ― የኦነግ ከፍተኛ አመራሩ አቶ ዐብዲ ረጋሳ በፍርድ ቤት ነጻ ተብለው ቢለቀቁም፣ በድጋሚ ታፍነው የደረሱበት አለማታወቁን ጠበቃቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ዐብዲ ረጋሳ በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ከዳለቲ እስር ቤት የተለቀቁ ቢሆንም፣ ከማረሚያ ቤቱ አንድ ኪሎ ሜትር ሳይርቁ በድጋሚ ታፍነው መወሰዳቸውን ነው ጠበቃው የተናገሩት፡፡

ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለሚዲያዎች እንደተናገሩት፣ ደንበኛቸው ከዚህ ቀደም በሦስት ወንጀሎች ተከሰው በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ነበር፡፡

ኦቶ ዐብዲ ረጋሳ የቀረበባቸው ክስ የቴሌኮም ማጭበርበር፣ የሽብር ክስ እና በ2008 በቦረና አካባቢ አንድ ሰው በእሳት እንዲቃጠል ትእዛዝ ሰጥተዋል የሚል የነበረ ሲሆን፣ በቀደሙት ሁለት ክሶች ከዚህ በፊት በነጻ እንዲለቀቁ ተበይኖ ነበር፡፡

የኦነግ አመራሩ ከሰሞኑ ብይን በተሰጠበት በሦስተኛው ክስ ማለትም፣ በቦረና አካባቢ አንድ ሰው በእሳት እንዲቃጠል ትእዛዝ ሰጥተዋል በሚለው ጉዳይ አቶ ዐብዲ በወቅቱ አስመራ እንደነበሩ ተናግረው ማስረጃዎችን አቅርበው መከራከራቸውን ጠበቃቸው ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት፣ አቶ ዐብዲ ረጋሳ ባቀረቡት ምስክር ራሳቸውን ተከላክለዋል በሚል በነጻ አሰናብቷቸዋል፡፡

ይህንኑ ብይን ተከትሎ ከእስር ቤት የተለቀቁት አቶ ዐብዲ ረጋሳ፣ ከሌላኛው የኦነግ ከፍተኛ አመራር ጋር ጀቤሳ ገቢሳ ጋር በድጋሚ ታፍነው ተወስደዋል የተባለ ሲሆን፣ ኋላ ላይ አቶ ጀቤሳ ገቢሳ ቢለቀቁም፣ እርሳቸው ግን የት እንደተወሰዱ እንዳልታወቀ ነው የተነገረው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img