Sunday, September 22, 2024
spot_img

አሜሪካ በካሾጊ ግድያ ግብጽ በነበራት ሚና ላይ ምርመራ እድታካሄድ ተጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 17፣ 2013 ― አሜሪካ የሳዑዲ ዐረቢያ ዜግነት ባለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ የግብጽ ባለሥልጣናት የነበራቸውን ሚና እንድትመረምር የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ ሰባት የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ጠይቀዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖቹ አሜሪካ የአገሯ ነዋሪ የነበረውን ጋዜጠኛ ግድያ አስመልክቶ የግብጽ ባለሥልጣናት የነበራቸውን ሚና የሚያመለክት የትኛውንም መረጃ ይፋ ታድርግ ነው ያሉት፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖቹ ባወጡት መግለጫ፣ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ አሜሪካ ከጀማል ካሾጊ ግድ ጋር በተገናኘ ግንኙነት አላቸው ያለቻቸው የደኅንነት ሰዎች ላይ ማእቀብ መጣሏንም አስታውሰዋል፡፡

የጋዜጠኞቸ መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ በበኩሉ፣ የአሜሪካ የደኅንነት ባለሥልጣናት እና ፖሊሲ አውጪዎች የግብጹ የደኅንነት መስሪያ ቤት አለቃ አባስ ከማልን በዋሽንግተን ለማግኘት ቀጠሮ መያዛቸውን ገልጧል፡፡

በሳዑዲ ልኡል መሐመድ ቢን ሰልማን ትእዛዝ እንደተገደለ በሚነገረው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጉዳይ ከሰሞኑ ዘገባ ይዞ የወጣው የአሜሪካው ኒውዮርክ ታይምስ፣ በግድያው ላይ የተሳተፉ አራት የሳዑዲ ዐረቢያ ዜጎች አሜሪካ ውስጥ ልዩ ሥልጠና መውሰዳቸውን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

ሠልጣኞቹ የግድያ ሥልጠናውን ያገኙት ከአሜሪካ መንግሥት ፍቃድ ከተሰጠው ድርጅት ነው የተባለ ሲሆን፣ ገዳዮቹን አሠልጥኗል የተባለው በ‹‹ሶርበርስ ካፒታል ማኔጅመንት›› ባለቤትነት የሚተዳደረው የግል ድርጅት እዚያው አሜሪካ የሚገኝ መሆኑም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ድርጅቱ የሳዑዲ ልኡላዊያን ጠባቂዎችን የሚያሰለጥን መሆኑንም ዘገባው አክሏል፡፡

ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለው በ2010 እንደነበር ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img