አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 17፣ 2013 ― ሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ጊመካ ቀበሌ ነዋሪ የነበረ የፓርቲው አባል እና የምርጫ ታዛቢ የነበሩት አቶ ግርማ ታደሰ ተደብድበው እንደተገደሉበት አሳውቋል፡፡
ፓርቲው፣ አባሉ እና የምርጫው ታዛቢው የነበሩት የአቶ ግርማ ታደሰ ገዳዮች ማንነት ለጊዜው ማንነታቸው አለመታወቁን ነው የገለጸው፡፡ ጉዳዮን ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት አሳውቆ ‹‹ምርመራ እየተካሔደ›› ነው ያለው ሕብር ኢትዮጵያ፣ በአባሉ ግድያ ሐዘኑን ገልጧል፡፡