Sunday, September 22, 2024
spot_img

የጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ገዳዮች አሜሪካ ውስጥ ልዩ ሥልጠና ማግኘታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ላይ የተሳተፉ አራት የሳዑዲ ዐረቢያ ዜጎች አሜሪካ ውስጥ ልዩ ሥልጠና ወስደው እንደነበር የአገሩ ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል።

ሠልጣኞቹ የግድያ ሥልጠናውን ያገኙት ከአሜሪካ መንግሥት ፍቃድ ከተሰጠው ድርጅት ነው የተባለ ሲሆን፣ ገዳዮቹን አሰልጥኗል የተባለው በ‹‹ሶርበርስ ካፒታል ማኔጅመንት›› ባለቤትነት የሚተዳደረው የግል ድርጅት እዚያው አሜሪካ የሚገኝ መሆኑም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ድርጅቱ የሳዑዲ ልኡላዊያንን ጠባቂዎችን የሚያሰለጥን ድርጅት ነው።

ጀማል ካሾጊ፣ በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ የሳዑዲ ዐረቢያውን ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ላይ ትችት ካስነበበ በኋላ በቱርክ በአሰቃቂ ሆኔታ መገደሉ መነገሩ ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛው ጀማል ካሾጊ የተገደለው 2010 ሲሆን፣ ከሞቱ ጀርባ የሳዑዲው ልዑል ሥማቸው ተያይዞ ይነሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img