Monday, September 23, 2024
spot_img

የኢትዮ ፎረም ባልደረባ ድብደባ እንደተፈጸመበት ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― በሚያቀርባቸው ወቅታዊ መረጃዎች ከፍተኛ ተከታታዮች ያሉት ኢትዮ ፎረም የተሰኘው የበይነ መረብ ሚዲያ ባልደረባ የሆነው አበበ ባዩ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት ሆስፒታል እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

የቀድሞው የኢቲቪ እንዲሁም አነጋጋሪ የነበረው ኢኤንኤን የተሰኘ ቴሌቪዥን ባልደረባ የነበረው አበበ ባዩ፣ ድብደባው በማን እንደተፈጸመበት የተሰማ ነገር የለም፡፡

ከሕወሃት ጋር ቅርበት አለው በሚል የሚነሳው ጋዜጠኛው የሚሠራበት ኢትዮ ፎረም፣ በሌላኛው የቀድሞ የኢቲቪ ጋዜጠኛ ኋላም በሳምንታዊው ፍትሕ መጽሔት አምደኝነት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የሚያዘጋጃቸው በትግራይ ቴሌቪዥን የሚቀርብ ዝግጅት ይተላለፍበት የነበረ ሚዲያ ነው፡፡

የጋዜጠኛውን ድብደባ ተከትሎም የበይነ መረብ ሚዲያው ባለፉት ሁለት ቀናት ዝግጅቶቹን ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡

ሚዲያው ስለ ባልደረባው ድብደባ የገለጸው ነገር ባይኖርም፣ ‹‹ከአቅማችን በላይ በሆነና ለጊዜው መግለጽ በማንፈልገው ችግር ምክንያት›› ፕሮግራማችንን አቋርጠናል ሲል አስፍሯል፡፡

የኦንላይን ሚዲያው ‹‹እጅጉን ያዘንበት›› ነው ያለውን የዝግጅቱን መቋረጥ ምክንያት፣ ለተከታታዮቹ በቅርብ እንድታውቁት አደርጋለሁ ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img