Friday, October 11, 2024
spot_img

ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት አሕመዲን ጀበል የምርጫ ድምጽ አግኝተዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― ጅማ ዞን ለመወዳደር ቢመዘገቡም አንድ ሳምንት ሲቀረው ራሳቸውን ማግለላቸውን ያሳወቁት አሕመዲን ጀበል፣ በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች ጥቂት ድምጾችን ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡

ይኸው የምርጫ ውጤት በተለጠፈበት ወቅት ይፋ መደረጉን የዘገበው ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው፡፡

ሆኖም ይህ ስህተት የተፈጠረው አሕመዲን ራሳቸውን ያገለሉት ከምርጫው ድምጽ መስጫ ቀን ጥቂት ቀናት ቀድሞ በመሆኑ፣ ምርጫ ቦርድ አዲስ የድምጽ መስጫ ወረቀት ማተም ስላልቻለ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል ዶይቸ ቨለ የጂማ ዞን ምርጫ አስተባባሪ አቶ ሸሪፍ አባ ገላን በበኩላቸው በምርጫው ዋዜማ ከምርጫው በይፋ ራሱን ያገለለ ዕጩ የለም ብለው መናገራቸውን አስታውሷል፡፡

ትላንት በሰባት ክልሎች የተካሄደው ስድስተኛው ምርጫ ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ከማለዳው አንስቶ ይፋ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img