Saturday, October 12, 2024
spot_img

ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ረሃብ የለም ሲሉ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህሕመድ ጦርነት ባለበት የትግራይ ክልል ውስጥ ረሃብ አለ መባሉን አስተባብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በትላንትናው ዕለት በሚወዳደሩበት በምርጫ ጣቢያ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ለሰነዘረችላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት በትግራይ ችግር መኖሩን ያመኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የመባሉንአስላበሚወዳደሩበትለተሰነዘረላቸበዚሁወቅትያመኑትጠቅላ ነገር ግን መንግሥት የሚፈታው ነው ብለዋል።

በጥቅምት ወር የተቀሰቀሰው የትግራይ ጦርነት አምስት ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ ፈላጊ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያስረዳል።

ከክልሉ ነዋሪዎች መካከል ከ350 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ደግሞ በረሃብ ቋፍ ላይ መሆናቸውን በቅርቡ የወጣ ተባበሩት መንግሥታት ግምገማ ሪፖርት ያሳያል።

ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በፀጥታው ምክር ቤት ዝግ ስብሰባ ላይ በትግራይ ረሃብ አለ ብለው መናገራቸውም ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img