Saturday, October 12, 2024
spot_img

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ጫት በአሳ እየተለዋወጡ ለመገበያየት ተስማሙ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― ኢትዮጵያና ሶማሊያ ጫት በአሳ እየተለዋወጡ ለመገበያየት መስማማታቸው ተነግሯል። በስምምነቱ መሠረት ከኢትዮጵያ ጫት የምትወስደው ሶማሊያ በምትኩ አሳ ትልካለች።

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዐብዱልፈታህ ዐብዱላሂ ሐሰን እና የሶማሊያ የአሳ ሚኒስቴር ዐብዲዛዝ ሐጅ በሽር አምስት ሺሕ ቶን ወደ አዲስ አበባ ማስጫናቸውን ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።

በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት የሶማሊያ መንግሥት ሰዎች ከኢትዮጵያ እና ቱርካዊያን የንግድ ሰዎች ጋር ጥንታዊው ዋርሼክ አካባቢ በማቅናት ከአሳ ምርት ጋር በተገናኘ ያለ አማራጮችን መመልከታቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

አሁን ከኢትዮጵያ ጋር ጫት በአሳ ለመለዋወጥ የተስማማችው ሶማሊያ፣ በ2018 ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጋር የሦስትዮሽ የትብብር ስምምነት መፈራረሟንም ዘገባው ጨምሮ አስታውሷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img