Friday, October 11, 2024
spot_img

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ምርጫው በፍትሐዊ መንገድ አለመካሄዱን ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― በአፋር ክልል የተወዳደረው የአፋር ሕዝብ ፓርቲ በትላንትናው እለት የተካሄደው ምርጫ በፍትሐዊ መንገድ አለመካሄዱን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አሠራር እንዲመጣ የበኩሉን ሙከራ ማድረጉን ያስታወሰው ፓርቲው፣ ሆኖም ይህ ሙከራው በትላናትናው እለት መና መቅረቱን አባላቶቹ እና ደጋፊዎቹን እወቁት ብሏል፡፡

ፓርቲው ዝርዝሩን እንደሚመለስበት በገለጸበት መግለጫው፣ አጠቃላይ የምርጫውን አካሄድ ውድቅ አድርጎታል፡፡

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ በአጠቃላይ የተካሄደውን ምርጫ በፍትሐዊነት ያልተካሄደ ነው ብሎታል፡፡

በትላትናው እለት በተካሄደው አገራዊ ምርጫ፣ የምርጫው አስፈጻሚ ምርጫ ቦርድ እኩለ ቀን ላይ በሰጠው መግለጫ፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከምርጫው አካሄድ ጋር በተገናኘ ችግሮች እንዳሉ ሲገልጽ፣ በአነስተኛ መጠን ቢገለጽም ችግር ታቶባቸውዋል ከተባሉት መካከል አንደኛው ክልል አፋር እንደነበር ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ለፓርቲው መግለጫ በምርጫ ቦርድም ሆነ በሌሎች አካላት የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img