Friday, October 11, 2024
spot_img

አብን የምርጫው ሂደት ከተለመደው የገዥው ፓርቲ ጫናና ህገ ወጥ ተግባር መላቀቅ አቅቶታል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 14፣ 2013 ― የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እየተካሄደ የሚገኘው ምርጫ ከተለመደው የገዥው ፓርቲ ጫናና ህገ ወጥ ተግባር መላቀቅ አቅቶት ህዝቡ ‹‹ተስፋ የጣለበትን የዴሞክራሲ ሂደት የሚያደበዝዝ ሆኖ አግኝተነዋል›› ሲል ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

አብን በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ተሳትፎ ሲያደርግ ምቹ የምርጫ ምህዳር አለ በሚል እምነት ሳይሆን ያሉ ችግሮች በሂደት ተፈትተው ቢያንስ የምርጫ ዕለት ህዝባችን በአንፃራዊነት ድምጹን በነፃነት ይሰጣል በሚል እምነት ነበር ብሏል፡፡

ፓርቲው በተለይ በአማራ፤ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች የታየውን የምርጫ ሂደት አስመልክቶ የተለያዩ የምርጫ ሂደት ግድፈቶችን በሚመለከት ተጨባጭ ማስረጃዎች እንደደረሰው ነው የገለጸው፡፡

በመሆኑም የአማራና የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት በየደረጃው ያሉ አመራሮች የምርጫ ህጉ በሚፈቅደው አግባብ ህጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡና ሰላማዊውን የምርጫ ሂደት ከማሰናከል እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img