Saturday, September 21, 2024
spot_img

በደቡብ እና በአማራ ታዛቢዎች መከልከላቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 14፣ 2013 ― ኅብረቱ ምርጫውን አስመልክቶ ባወጣው ቅድመ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ከምርጫው ጋር በተገናኘ አሳሳቢ ያላቸው 118 ኹነቶችነ ተቀብሏል፡፡ ከዚህ ውውጥ በርካታ አሳሳቢ ኹነቶች የተከሰቱት በአማራ እና በደቡብ ክልል ውስጥ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

እነዚህ አሳሳቢ ናቸው ያላቸው ኩነቶች ታዛቢዎች ምርጫ እንዳይታዘቡ መከልክል እና የምርጫ ቁሳቁስ መጓደል መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ከ2 ሺሕ ከሚበልጡ የምርጫ ተሰብስቧል ባለው መረጃ መሠረት በግምት 93 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ታዛቢዎች ወደ ምርጫ ጣቢያው ሲደርሱ በቦታው መገኘታቸውን የገለጸ ሲሆን፣ የኅረቱ ታዛቢዎች በተገኙበት የምርጫ ጣቢያዎች በተገኘው ሪፖርት መረት ወደ 98 በመቶ የሚሆኑት ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት የተጀመረው ከጠዋቱ አንድ ሰአት በፊት መሆኑን አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል በታዛቢዎች በተገኘው መረጃ መሠረት 11 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች የተዋቀሩት በፖሊስ ጣቢያ፣ በፖለቲካ ፓርቲ ሕንጻ፣ ወይም በወታደር ካምፕ ሲሆን፣ እነዚህ ሥፍራዎች በምርቻ ቦርድ መመሪያ መሠረት የተከለከሉ ናቸው ብሏል፡፡

ከምርጫ ጣቢያዎች መከፈት በተያያዘም መረጃ ያወጣው ኅብረቱ፣ 99 በመቶ ያህል በሚሆኑት ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ከመታሸጋቸው በፊት ባዶ መሆናቸው በግልጽ እንደሚታይ ነው ያመለከተው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img