Friday, October 11, 2024
spot_img

የምርጫ መረጃ

ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ ተከፍተዋል የተባሉ ምርጫ ጣቢያዎች መራጮችን ማስተናገዳቸው ተሰምቷል፡፡ እነዚህ ምርጫ ጣቢያዎች ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድሬዳዋ ከተማ ከእውቅናዬ ውጭ ተከፍተዋል በሚል ያገዳቸው ነበሩ፡፡

የምርጫ ጣቢያ መለያ ሳይወስዱ ተጨማሪ ጣቢያ በመክፈታቸው ምክንያት ምርጫ ቦርድ አግዷቸው የነበሩት ጣቢያዎቹ በትላንትናው ዕለት ድምጽ እንዲሰጥባቸው ቦርዱ ወስኗል፡፡

የምርጫ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችና ኅብረተሰቡ ባቀረቡት ቅሬታና ጥያቄ መሰረት መራጮችን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት ከግምት በማስገባት ምርጫ ቦርድ ስድስቱ ጣቢያዎች ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል።

መራጮች ከዚህ በፊት የተመዘገቡበትን የምርጫ ካርድ በመያዝ እንደ አዲስ እየተመዘገቡ መምረጥ እንደሚችሉ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img