Friday, October 11, 2024
spot_img

የምርጫ መረጃ

– ‹‹እነ ጃዋር የሌሉበት ምርጫ አንፈልግም››

በአዳማ የምርጫ ጣቢያ እንደተበጠበጠ ተሰማ፡፡ በአዳማ ከተማ ጉርሙ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ አምባጓሮ መፈጠሩ ተሰምቷል፡፡

አምባጓሮውን የፈጠሩት እንደማንኛውም መራጭ ሰልፋቸውን ጠብቀው ድምጽ የሚሰጥበት ጣቢያ ውስጥ የገቡ ወጣቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ወጣቶቹ የምርጫ ኮሮጆውን ጨምሮ ሌሎችንም ወረቀቶች በመበታተን ብጥብጥ ለመፍጠር መሞካራቸውን የዐይን እማኞች ነግረውኛል ብሎ አዲስ ዘይቤ ዘግቧል፡፡

ወጣቶቹ ‹‹እነ ጃዋር የሌሉበት ምርጫ አንፈልግም›› ሲሉ ተደምጠዋል ተብሏል፡፡ ወጣቶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ምርጫ ጣቢያው መራጮችን ማስተናገድ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img