Friday, October 11, 2024
spot_img

የምርጫ መረጃ

በደቡብ ክልል ኡባ ደብረ ፀሐይ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ የምርጫ ሳጥን መሰረቁን የምርጫ ቦርድ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ኡባ ደብረ ፀሐይ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ አንድ የምርጫ ሳጥን መሰረቁን አስታውቋል፡፡

የቦርዱ ሰበሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በሰጡት መግለጫ የአማራ ክልልን ጨምሮ በአንዳንድ ክልሎች መራጮች እንዳይመርጡ የማስፈራሪያ እና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሰብሳቢዋ ተቀባይነት የለውም ያሉት ይህ ድርጊት፣ በውጤቱ ላይ የሚያመጣው ክፍተት ስለሚኖር በፍጥነት እንዲቆም አሳስበዋል፡፡

ድርጊቱን ለክልሉ ለአስተዳደሮች ማስታወቃቸውን የገለጹት ብርቱካን፣ በዚህ መጠን የሚገድብ የተመታዘብ ሂደት ካለ መጨረሻ ላይ ቦርዱ ሂደቱን ሲገመግም ውጤት ላይ ተጽኖ እንዳለውና ቦርዱ ውጤት ላመጽቅ ይህንኑ ከግንዛቤ እንደሚያስገባ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መግለጫ ወቅት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርተካን ሚዴቅሳ በአዲስ አበባ 9 ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች በሰዓቱ ሳይገኙ ቀርተው ጣቢያዎቹ ሳይከፈቱ ቆይተው እንደነበር ያመለከቱ ሲሆን፣ አስፈጻሚዎች ባልተገኙባቸው 9 የአዲስ አባባ ምርጫ ጣቢያዎች 27 አስፈጻሚዎች ተልከው ምርጫው ተጀምሯል ብለዋል፡፡

ሰብሳቢዋ በአዲስ አበባ በሌላ አንድ ምርጫ ጣቢያ የመራጮች መዝገብ መጥፋቱን፤ ይህም እንደሚጣራና መራጮችም ባወጡት ካርድ መምረጥ ይችላሉ ብለዋል፡፡

በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የቁሰቀስ እጥረት ማጋጠሙን በመጠቆምም፣ እጥረቱ አታሚው ከሰጠነው ትዕዛዝ ውጪ መቶ መቶ የማሸግ፣ በ50 አሽጎት ስለነበረ ጉድለት አጋጥሟል፣ ጉድለቱ በክልል እንጂ በተወካዮች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ አላጋጠመም ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በመግለጫው በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ አባላት መምረጥ አለመምረጣቸውን የጠጠየቁት ሰብሳቢዋ፣ ምርጫ ቦርድ በእስር ቤት የመራጮች ጣቢያ አለማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በመግለጫው በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ አባላት መምረጥ አለመምረጣቸውን የጠጠየቁት ሰብሳቢዋ፣ ምርጫ ቦርድ በእስር ቤት የመራጮች ጣቢያ አለማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img