Friday, October 11, 2024
spot_img

የምርጫ መረጃ

ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘቅዴ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ከድምጽ መስጠት ሒደት በኋላ ለሚዲያዎች እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በአብዛኛው አገር ውስጥ ባለመኖራቸው መምረጥ እንዳልቻሉ አስታውሰው፣ በዚህኛው ዙር ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጻቸውን መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ራስ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ምርጫ ጣቢያ 04/05 ለመምረጥ በተገኙበት ወቅት የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች በሥፍራው ሆነው ሂደቱን ተከታትለዋል።

ለሚዲያዎች የተናገሩት የኅብረቱ ታዛቢ ቡድን ኃላፊ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እየተካሄደ የሚገኘው ምርጫ ከቀደሙት በሕዝብ ተሳትፎም ሆነ በእጩዎች ብዛት የተሸ መሆኑን መናገራቸውን አሐዱ ራዲዮ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img