Friday, October 11, 2024
spot_img

ዜጎች ድምፃቸውን ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲወጡ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ሰኔ 13፣ 2013 ― ሁሉም ዜጎች ነገ ድምፃቸውን ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲወጡ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ሰኔ 14፣ 2013 ከሚካሄደው 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በፊት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለመስጠት እንዲንቀሳቀሱ የተደረገውን የመጨረሻ ዝግጁነት የሚገመግም ምክክር መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ደኅንነት ስትራቴጂ ማዘዣ ዛሬ ጠዋት ባደረገው ምክክር የጸጥታ ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሠማራ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ድጋፍ ለተለዩ እና ለሚከሠቱ አደጋዎች ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ተመልክቷል።

“ሁሉም ዜጎች ነገ ድምፃቸውን ለመስጠት ሲወጡ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ አበረታታለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግሥት ለሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ቀን በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img