Sunday, October 6, 2024
spot_img

በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምርጫ ለ171 የፓርላማ ወንበር በሚደረገው ፉክክር ብልፅግና ፓርቲ በ104 ያህሉ ላይ ብቻውን እንደሚወዳደር ታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ሰኔ 13፣ 2013 ― ነገ በሚደረገው ምርጫ በኦሮሚያ ክልል ለ171 የፓርላማ ወንበር በሚደረገው ፉክክር ብልፅግና ፓርቲ በ104 ያህሉ ላይ ብቻውን እንደሚወዳደር ቁጥሮች ያመለክታሉ።

በተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ቅስቀሳ ፈታኝ እንደነበር ስሞት ሲቀርብበት በነበረው የኦሮሚያ ክልል፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአብዛኞቹ ቦታዎች ላይ አይወዳደሩም፡፡

ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ 60 በመቶ ገደማና ከዚያ በላይ፣ ያለተወዳዳሪ ነው እንደቀረበ ነው የታወቀው።

በኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ ለ171 የፓርላማ ወንበር የተመዘገበው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ 268 ተወዳዳሪዎች ይፎካከራሉ፡፡

በሌላ በኩል ለ128 የፓርላማ ወንበሮች፣ በአጠቃላይ ከ740 በላይ ተወዳዳሪዎች ይፎካከራሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ወንበር፣ በአብዛኛው 5 እና ከዚያ በላይ ተወዳዳሪዎች ይገኛሉ።

ብርቱ ፉክክል ይኖርባታል ተብላ በምትጠበቀው አዲስ አበባ፣ ለከተማ ምክር ቤትና ለፓርላማ ብልፅግና፣ ኢዜማና ባልደራስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋለ ተብሎ እየተነገረላቸው ይገኛል።

በአዲስ አበባ፣ ለእያንዳንዳንዱ የፓርላማ ወንበር፣ 7 ወይም ከዚያ በላይ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ፡፡

በነገው እለት በሚደረገው አገር አቀፉ ምርጫ ትግራይ ክልል ከያዘው 38 መቀመጫ ውጭ ከአጠቃላዩ የፓርላማ መቀመጫ ምርጫው የሚከናወንባቸው የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 445 መሆኑን ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ አይዘነጋም።

በአሁኑ አገር አቀፍ ምርጫ በአጠቃላይ 509 የፓርላማ መቀመጫዎች እንዳሚገኙ የጠቆመው ምርጫ ቦርድ፣ ቀሪዎቹ 64 የሐዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ድምጽ የሚሰጥባቸው ጳጉሜ 1፣ 2013 መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img