Sunday, October 6, 2024
spot_img

የምርጫ ቦርድ መልዕክት

አንድ መራጭ ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምን ያህል እጩዎችን መምረጥ ይችላል?

ለክልል ወይም ለከተማ ም/ቤት መቀመጫ አንድ መራጭ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት እንደየምርጫ ክልሉ ይለያያል ። አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 1 እጩ፣ እንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 3 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ላይ 9 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 14 እጩዎች ወይም ሌላ ቁጥር ያለው የመቀመጫ ብዛት ሊኖራቸው ይችላል።

ብዛቱ የሚወሰነው የምርጫ ክልሉ በክልል ም/ቤቱ ባለው የመቀመጫ ቁጥር ብዛት ነው ። በመሆኑም አንድ መራጭ በክልል ም/ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ መምረጥ የሚችለው የዕጩዎች ብዛት በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ከላይ ተፅፎ ይገኛል። በዚህም መሰረት አስፈጻሚዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጡ ለመራጩ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ እስከ ስንት እጩ መምረጥ እንደሚችል ያስረዳሉ።

ሆኖም ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አንድ ዕጩ ብቻ የሚመረጥ ይሆናል። ስለዚህም ከዚህ ቁጥር ገደብ በላይ ምልክት የተደረገባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አይኖራቸውም።

በመሆኑም ድምፅዎን ሲሰጡ በወይን ጠጁ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወረቀት አንድ በክልል ምክር ቤት ወረቀት ደግሞ ወረቀቱ ላይ በተጻፈው እና ምርጫ አስፈጻሚው በሚነግርዎ ቁጥር መሰረት መሆኑን አይርሱ። ከተፈቀደው የእጬ ቁጥር በላይ ምልክት አያድርጉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img