Friday, October 11, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን ትብብር ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― በመጪው ሰኞ የሚደረገውን የምርጫ ድምጽ አሳጣጥ ለማስፈጸም የመጨረሻ ሰአት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ እገዛ ጠይቋል፡፡

በቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ ቦርዱ በመጪው ሰኞ ለሚደረገው ምርጫ ቁሳቁስ አስቀድሞ መድረሱን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን ገልጧል፡፡

ነገር ግን ‹‹በተለያዩ ሁኔታዎች ጥቂት ቦታዎች ላይ ሳንካዎች ቢገጥሙ በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት ይቻል ዘንድ›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት መንግሥት ‹‹የሚያዝበት በማንኛውም ተቋም ስር የሚገኝ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አቅም (የየብስ እንዱሁም ሌሎች)፣ እንዲሁም የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ የሚያስፈልግ ተጠባባቂ የሕግ አስፈጻሚ ኃይል ለዚህ አገራዊ ሰላማዊ እና ሕጋዊ ኦፕሬሽን ቅድሚያ በመስጠት ፍጥነትን የተላበሰ ምላሽ ለቦርዱ እንዲሰጡ አስፈላጊውን መመሪያ እንዲስተላልፉ›› በማለት የምርጫውን ሕግ አንቀጽ 161 አጣቅሶ ምርጫ ቦርድ እገዛውን ጠይቋል፡፡

ቦርዱ በማሳረጊያው ከዚህ ቀደም ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ለተደረገለት ትብብር ምስገጋናዬ ይድረስ ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img