Friday, October 11, 2024
spot_img

የሲኤንኤን እና አልጀዚራን ጨምሮ 89 ጋዜጠኞች ምርጫውን ለመዘገብ አዲስ አበባ ገብተዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― ከነገ በስትያ ሰኞ ሰኔ 14 የሚካሄደውን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለመዘገብ የአልጀዚራ እና ሲኤንኤን ጨምሮ ሰማንያ ዘጠኝ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

አሃዙ እስከ ትላንት ድረስ ምርጫውን ለመዘገብ ፍቃድ ያገኙ የ29 የውጭ አገራት ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ብዛት ብቻ መሆኑን የጠቀሰው ባለሥልጣኑ፣ በቀጣይም ጥያቄ አቅርበው ለመዘገብ የሚገቡትን ዝርዝር ይፋ እንደሚያደርግ ነው የገለጸው፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ ጋዜጠኞቻቸውን ከወከሉ የውጭ ሚዲያዎች መካከል ከአልጀዚራ እና ሲኤንኤን በተጨማሪ ቢቢሲ፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ሬውተርስ፣ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ፣ ቪ.ኦ.ኤ፣ አሶሽየትድ ፕረስ፣ ዶቼ ዌሌ፣ ፋይናንሻል ታይምስ እና ሲቢኤስ ይገኙበታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img