Sunday, September 22, 2024
spot_img

ሳዑዲ ዐረቢያ ከኢትዮጵያ የሐጅ ሥርዐት ለመፈጸም የሚጓዙ ሰዎችን አልቀበልም ማለቷ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 11፣ 2013 ― ሳዑዲ ዐረቢያ በኮቪድ19 ወረርሽኝ ሰበብ በያመቱ ለሚካሄደው ሥነ ሥርዐት ከኢትዮጵያ የሚደረግ ጉዞን እንደሰረዘች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቋል፡፡

የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚና የሐጅና ኡምራ ጉዞ አስተባባሪ ዶክተር ጄይላን ከድር ገመዳ ነግረውኛል ብሎ ኢዜአ እንደዘገበው፣ በዓለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘንድሮ ወደ ሐጅ የሚደረግ ጉዞ ተሰርዟል፡፡

አስተባባሪው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦችን ለማስተናገድ ዝግጅት ሲያደርግ ቢቆይም፣ የሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ይፋ ባደረገው መመሪያ አገሪቷ ተጓዦችን እንደማትቀበል አሳውቋል ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ይህን በመረዳት ለፓስፖርትና ለተለያዩ የሐጅ ጉዳዮች የሚያደርገውን ዝግጅት በማቆም ከእንግልትና ከአላስፈላጊ ወጪ እንዲታቀብም ዶክተር ጀይላን መክረዋል።

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት የዘንድሮውነ የሐጅ ሥነ ሥርዓት በአገሪቷ ዜጎችና በሳዑዲ ዓረቢያ በሚኖሩ ውስን የውጭ አገራት ዜጎች ብቻ እንደሚከናወን መግለጹንም ነው ዶክተር ጄላን ያስረዱት፡፡

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት በየዓመቱ ስምንት ሺሕ ያህል ዜጎች ለሐጅና ኡምራ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ይጓዙ እንደነበር ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img