Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ምዕራብ ሸዋ ውስጥ አስር የመንገዶች ባለሥልጣን ሠራተኞች በታጣቂዎች ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 11፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በመንገድ ግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ አስር ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል፡፡

የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ እንደተናገሩት ጥቃቱ በዞኑ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ሎያ ጎዳኔ ቀበሌ ውስጥ ከትላንት በስትያ ረቡዕ ሰኔ 9፣ 2013 አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ ነው የተፈጸመው።

አቶ ዲሪርሳ በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት የፌደራልና የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ባለሙያ የሆኑ ዘጠኝ ሰዎች እና የቀበሌው ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ተገኝ በበኩላቸው የባለሥልጣኑ ባልደረቦች የሆኑ አስር ሰዎች በታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን አረጋግጠዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዜና ተቋሙ ከአንድ የባለሥልጣኑ ባልደረባ ተረድቻለሁ እንዳለው ሠራተኞቹ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የዓለም ገና ዲስትሪክት ባልደረቦች ሲሆኑ፣ የተበላሸ መንገድ ጠግነው አመሻሽ ላይ ሲመለሱ መኪናቸው በታጣቂዎች እንዲቆም ተደርጓል፡፡

በታጣቂዎቹ ከተገደሉት ሰዎች መካከል መሃንዲስ፣ ሾፌር፣ የቡል ዶዘር ቴክኒሺያንና በተለያዩ ሙያዎች የመንገድ ግባታ ባለሙያዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

አቶ ዲሪርሳ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አስራ አንድ የመንገድ ግንባታ ባለሙያዎች መካከል ከግድያው ያመለጡት ሁለቱ “በአካላቸው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤ ደህና ናቸው” ብለዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪው ጥቃቱን የፈጸመው ‹‹ኦነግ ሸኔ›› የተባለው ቡድን እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፤ ስለተፈጸመው ግድያ ከቡድኑ በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img