Friday, October 11, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያጓጓዝኩት የጦር መሳሪያ የለም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች የጦር መሳሪያ አጓጉዟል የሚል አሉባልታ እየተሰራጨብኝ ነው ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ወደ የትኛውም የአገሪቱ ክፍል መሳሪያ አላጓጓዝኩም ሲል በትዊተር ገጹ ላይ አሳውቋል።

አየር መንገዱ በመግለጫው የጦር መሳሪያ አጓጉዝልኝ ተብዬ ተጠይቄ አላውቅም ሲል አክሏል።

የአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት መልካም ሥሜን ለማጉደፍ ቆርጦ በመቀጠል ፎቶዎችን አሠራጭተዋል ሲልም ተፈጽሞብኛል ያለውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞቼ፣ አጋሮቼ እና ሁለም ባለድርሻዎች ይህንኑ እወቁት ነው ያለው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img