Friday, October 11, 2024
spot_img

ሻሸመኔን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚሠሩ ኃይሎችን እንደማይታገስ የከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― ሻሸመኔ ከተማ ከዚህ ቀደም የተከሰተውን ዐይነት ትርምስ እና ሥርአት አልበኝነት ዳግም ለመፍጠር የሚያስቡ ኃይሎች አስቀድመው ሐሰተኛ መረጃን እያሰራጩ በመሆናቸው ነዋሪው ራሱን ካልተረጋገጠ ወሬ እና አሉባልታ እንዲቆጥብ የሻሸመኔ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል፡፡

የከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆታ እንደተናገሩት ቆይታ ከተማዋ አሁን ዳግም ወደ ቀደመ እና የሞቀ እንቅስቃሴዋ መመለሷን በማመልክትነዋሪው በስማ በለው የሚነገሩትን ሁሉ እየሰማ መረበሸ የለበትም ብለዋል፡፡

ከተማችን ሻሸመኔ በጣም ሰላም ናት ያሉት አቶ ስንታየሁ፣ ስድስተኛ ጠቅላላ ምርጫም በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማዋ የጸጥታ ኃይል፣ የክልል እና የመከላከያ ሰራዊት በጋራ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን ሠርተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህዝቡን ለማወከ የሚደረጎ ጥረቶችን እንቅስቃሴዎች በተመለከተ የከተማዋ ነዋሪ ለፖሊስ ጥቁማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

እኛ የምንሰራው ለሕዝቡ ነው ስለዚህ ምንም ዐይነት ችግር ዳግም በከተማችን አይከሰትም ሲሉ አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተነሳ ሁከት ከፍተኛ ውድመት ካስተናገዱ ከተሞች መካከል አንደኛዋ ሻሸመኔ መሆኗ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img