Thursday, November 21, 2024
spot_img

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን ቃለ ምልልስ መተላለፍ ተቃወሙ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ‹‹የምርጫ 2013 ቅስቀሳ ካበቃ እና የጥሞና ጊዜ ከተጀመረ በኋላ›› የሚደረግ ነው ያሉትን የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆነው ፋና ቴሌቪዥን ሊያስተላልፍ ቀጠሮ የያዘለትን የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ቃለ ምልልስ ተቃውመዋል፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከትላንት በስትያ ባሰራጨው መልእክት ከድምጽ መስጫ ቀን በፊት ያሉ አራት ቀናት የጥሞና መሆናቸውንና በነዚህ ቀናት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ መጠይቆችን ማድረግ መከልከሉን አሳውቆ ነበር፡፡

እነዚህ አራት የጥሞና ቀናት ዛሬ የጀመሩ ቢሆንም፣ ፋና ቴሌቪዥን የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ቃለ ምልልስ ነገ ዐርብ ምሽት ሦስት ሰአት ላይ ስለማስተላልፍ ተመልካቾቼ ይጠብቁኝ በማለት ማስታወቂያ አስነግሯል፡፡

ይህን የተቃወሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ‹‹የገዢው ፓርቲ ዕጩ በፋና ቴሌቭዥን ያደረጉት ቃለ ምልልስ በጥሞና ጊዜ ውስጥ እንዳይተላለፍ በማገድ ለምርጫው ፍትሐዊነት የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት እንዲወጡ እጠይቃለሁ›› ሲሉ በትዊተር መልእክታቸውን ሰደዋል፡፡

ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በተጨማሪ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች መተላለፍ የለበትም በሚል ተቃውሞ እያስተናገደ የሚገኘውን ቃለ ምልልስ አስተላልፋለሁ ያለው ፋና፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንም ሆነ ምርጫ ቦርድ ይህ ዘገባ እስከተሰናዳበት ሰአት ድረስ ያሉት ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img