አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በመጪው ሰኞ የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቅርበዋል።
ጉባኤው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች ባሉበት የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም አካላት ጠብ አጫሪ ከሆኑ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡና ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ኢትዮጵያውያን በተለይ ወጣቱ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል፡፡
የምርጫው ውጤት በሚመለከተው አካል እስኪገለጽ ድረስ፣ ሁሉም በትዕግስት ሊጠባበቅ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ምርጫውን የሚያስተባብሩ አካላትም የምርጫውን ሂደት በፍጹም ግልጸኝነት እንድያስተባብሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡