Sunday, September 22, 2024
spot_img

የተመድ የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ በትግራይ ያለው ሁኔታ ከታሰበው በላይ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ በትግራይ ያለው ሁኔታ ከታሰበው በላይ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን የፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ላይ ባደረገው የዝግ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡

በስብሰባው ላይ በትግራይ ያለውን ቀውስ ረሃብ በማለት ለመፈረጅ አንዳንዶች ቢጠነቀቁም ኃላፊው ግን ያለ ምንም አሻሚ ቃል ‹‹ረሃብ አለ›› ማለታቸውን ቢቢሲ የኃላፊውን ንግግር አግኝቼ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ኃላፊው በክልሉ ስላለው ሁኔታም ሲናገሩ ‹‹የእርዳታ ሠራተኞች ተገድለዋል፣ ተዋክበዋል፣ ተደብብድበዋል እንዲሁም በረሃብ ለሚሰቃዩ ሰዎች እርዳታ እንዳያደርሱ ከመታገዳቸው በተጨማሪ ተመልሰው እንዳይመጡም ተነግሯቸዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በምግብ እጦት የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ሪፖርት አድርጓል›› ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

በቅርቡ የትግራይን የምግብ ሁኔታ የገመገመ ሪፖርት አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ ጉዳትን እንደሚያስከትል ቢፈርጅም፣ ኃላፊው ግምገማው ያለውን የከፋ ሁኔታ አቅልሎ እንዳየም ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን በክልሉ በተወሰነ መልኩ እርዳታ ማድረስ ቢቻልም፣ ማርክ ሎውኮክ እንደሚሉት ግን ‹‹በአስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሚሊዮኖች እርዳታ እያገኙ አይደሉም››፡፡

ከሰሞኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጠው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በትግራይ ረሃብ አለ የሚለውን እንደማይቀበል የገለጸ ሲሆን፣ መንግሥት በክልሉ ውስጥ በበቂ ሁኔታ እርዳታ እያከፋፈለ መሆኑንም አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img