Monday, September 23, 2024
spot_img

ፌስቡክ መንግሥት በድብቅ ያሰማራቸው በርካታ አካውንቶችና ገጾች መሰረዙን አስታወቀ

– በድምሩ በእርምጃው በ175 አካውንቶች ተሰርዘዋል

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― የፌስቡክ ኩባንያ መንግሥት በድብቅ ያሰማራቸው እና በተቀናጀ መንገድ የሚሠሩ ነበሩ ያላቸውን 64 የፌስቡክ አካውንቶች፣ 52 ገጾች፣ 27 የቡድን ስብስቦች እና 32 የኢንስታግራም አካውንቶችን መዝጋቱን አስታውቋል፡፡

ከእነዚህ ከተዘጉ ገፆች መካከል አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሚሆኑት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ተከታይ የነበራቸው ሲሆን፣ ከ760 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሚሆኑት ግሩፖች አባል የሆኑባቸው እንደነበረ ድርጅት አሳውቋል።

እነዚህን አካውንቶች ብዙ ተከታይ እንዲያፈሩ ከ6 ሺሕ ዶላር በላይ በድምር ወጪ መደረጉም ተገልጧል።

በተለይ አማርኛ ቋንቋ ይጠቀሙ ነበር የተባሉት አካውንቶቹ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር የተያያዙ አዎንታዊ ጽሑፎችን ያትሙ እንደነበር እንዲሁም ኦነግ፣ ኢዴፓ እና ሕወሓትን ጨምሮ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ነቀፌታ ይሰነዝሩ እንደነበር ኩባንያው ገልጧል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችውን ማእቀብ የሚነቅፉ ጽሑፎች እንደነበሯቸውም ነው ያሳወቀው፡፡

አካውንቶቹ ከኢትዮጵያ ደኅንነት መረብ ኤጀንሲ (ኢንሳ) ውስጥ ካሉ አንዳንድ ግለሰቦች ጋር የተገናኙ መሆናቸውንም የኩባንያው መግለጫ አመልክቷል። ውተርስ ጉዳዩን አስመልክቶ ለኢንሳ ማብራሪያ ቢጠይቅም መልስ ሳይሰጠው እንደቀረ ዘግቧል።

ኩባንያው እርምጃውን መውሰዱን ያሳወቁት የፌስቡክ የደህንነት ፖሊሲዎች ኃላፊ ናትናኤል ግሌቸር አካውንቶቹ እንዲዘጉ የተደረጉት በመጪው ሰኞ ከሚደረገው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ መሆኑን ገለጸዋል፡፡

አካውንቶቹን ኩባንያው ባደረገው የውስጥ ክትትል እና ምርመራ እንደደረሰባቸው የገለጹት ናትናኤል ግሊቸር፣ አሁንም ቢሆን ክትትሉ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ፌስቡክ ባለፈው ወር በግብጽ መንግሥት አማካይነት ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት ለመቀስቀስ የሚጥሩ የፌስቡክ ገጾችን ማስወገዱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ፎቶ፡ የተዘጉት አካውንቶች ካተሟቸው ይዘቶች መካከል

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img