Wednesday, December 4, 2024
spot_img

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ ጳጉሜ 1 ቀን እንዲካሄድ ተወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 9፣ 2013 ― የምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ሕዝበ ውሳኔ ከምርጫው ጎን ለጎን ሰኔ 14 ይካሄዳል ቢባልም በመጨረሻ ግን ጳጉሜ 1፣ 2013 እንዲካሄድ መወሰኑን ይፋ አድርገዋል፡፡

ሕዝበ ውሳኔ የሚደረግባቸው አካባቢዎች አስተዳደሮች ማለትም የከፋ፣ ዳውሮ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞና የሸካ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ አስተዳደሮች ሕዝበ ውሳኔው ከምርጫው ጋር አብሮ አለመደረጉን በተመለከተ ተቃውሞ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ዞኖቹ ቅሬታ አቅርበው እንደነበር ያነሱት ወ/ት ሶሊያና፤ ብዙ ከመራጮች ምዝገባ ጋር ተያይዞ የተነሱትን ጥያቄዎችን ለመፍታት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ምርጫውን እና የሕዝበ ውሳኔውን የግድ ጳጉሜ 1፣ 2013 እንዲደረግ ተወስኗል ብለዋል፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img